ሜሞሪ ባንዳ የህይወት እጣዋ ከእህቶቿ የተለየ ሆነ እህቷ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወደ ባህላዊው ‹የስልጠና ካንፕ› ተላከች ሴት ህጻናትን ‹ወንድን በጾታ ግንኙነት እንዴት ማርካት እንደሚቻል› የሚሰለጥኑበት ካንፕ በዛም በ11 አመት ጨቅላ እድሜዋ ለእርግዝና ተዳረገች፡፡ ባንዳ ግን ባለመሄድ አቋሟ ጸናች ከዛ ይልቅ ሌሎችን በማደራጀት ለማህበረሰቡ መሪዎች የትኛዋም ሴት ህጻን 18 አመት ሳይሞላት በግዴታ መዳር እንደሌለባት በህግ ደረጃ እንዲጸድቅ ጥያቄ አቀረበች በዚህ አላቆመችም በአገር አቀፍ ደረጃ ትግሏን ገፋችበት.... ለመላው ማላውያን ሴት ህጻናት አመርቂ ውጤትም አስመዘገበች፡፡
